Business ID 2890166

አዲስና ቀላል የእንግሊዝኛ መማሪያ መጽሐፍ

Nifaas Silk Laaftoo Finfinnee ላፍቶ ኢንደስትሪ መንደር
About Us

ከዚህ ቀደም እንግሊዝኛን በመደበኛ ትምህርት ቤቶች ውስጥ ለብዙ አመታት ተምረው ነበር? ነገር ግን አሁንም ድረስ ምንም አይነት እንግሊዝኛ በወጉ አይናገሩም
ይህ የብዙ ሰዎች ችግር ነው። ብዙ የእንግሊዝኛ ቃላትን ሸመደዱ ማለት እንግሊዝኛ መናገር ይችላሉ ማለት አይደለም! እንግሊዝኛ ንግግር ለመቻል ትክክለኛውን የእንግሊዝኛ መማሪያ ዘዴ (ሳይኮሎጂ) ማወቅና መተግበር ያስፈልጋል። በዚህች መጽሐፍ ውስጥ እንግሊዝኛን ባጭር ጊዜ የሚማሩበትን ዘዴ (ሳይኮ) ያውቃሉ!
ብዙ ሰው እንግሊዝኛ ለመልመድ የእንግሊዝኛ ቃላትን ብቻ መሸምደድ በቂ ይመስለዋል፤ ነገር ግን አንድ ተማሪ ለአመታት ያህል ሙሉውን ድክሽነሪ ቢሸመድድ፣ ወይም በመደበኛ ትምህርት ቤት ውስጥ ተምሮ ቢያልፍ እንግሊዝኛ መናገርም ሆነ መረዳት አይችልም፤ ምክንያቱም የሸመደደውን ቃል የቃሉን አገባብ፣ የቃሉን ምድብና የቃሉን ትክክለኛ አወጣጥ (Pronunciation) አያውቅም! እንግሊዝኛውን የተማረው በተሳሳተ መንገድ ነው። ያስተማሩት መምህራኖችም እንግሊዝኛ የሚችሉ አይደሉም። አፉንና ምላሱን ንግግር አላሰለጠነም። ጆሮውንም ማዳመጥ አላስለመደውም። ረጃጅም የእንግሊዝኛ ፅሁፎችን ማንበብ አለመደም። በዚህ ምክንያት የሸመደደው ቃላት ሁሉ ትርጉም የለሽና ግራ አጋቢ ሂደቱም ተስፋ አስቆራጭ ይሆንበታል!
በዚህች መጽሐፍ ውስጥ እንግሊዝኛን ባጭር ጊዜ ውስጥ ለመማር የሚያስችሉዎትን ዘዴዎች ያገኛሉ! ብዙ ሰዎችም እዚች መጽሐፍ ውስጥ የተዘረዘሩትን ዘዴዎች ተግባራዊ በማድረግ እንግሊዝኛን በቀላሉ መማርና ማወቅ ችለዋል።
እንግሊዝኛን ቃላት በመሸምደድ ብቻ መማር ምንም የረባ ለውጥ አያመጣም። ስለዚህ ሌሎች አዳዲስ የእንግሊዝኛ መማሪያ ዘዴዎችን ማወቅ ያስፈልጋል። ጥሩ የእንግሊዝኛ ተናጋሪ ለመሆን ቃላትን ከመሸምደድ ባሻገር ብዙ ክህሎቶችን ማዳበር ያስፈልጋል፤ ከነዚህም መካከል የማዳመጥ ክህሎት አንዱና ዋነኛው ነው። እንዲሁም የእንግሊዝኛ ሀረጎችን፣ ሙሉ አረፍተ ነገሮችንና ትክክለኛ አነጋገራቸውን ማወቅ ያስፈልጋል። ለዚህም ነው እንግሊዝኛን ከራሳቸው ከፈረንጆቹ አንደበት መስማትና መማር አስፈላጊ የሆነው። ይህን ለማድረግ ደግሞ በቀላሉ የእንግሊዝኛ ፊልሞችን መመልከት በቂ ነው። መጽሐፏ ፊልሞችንና ዘፈኖችን በመጠቀም እንደት እንግሊዝኛን በቀላሉ መማር እንደሚችሉ በግልፅ ታስረዳዎታለች።
በመደበኛ ት/ቤት ተምረው ወደ ገሀዱ አለም ሲወጡ፦
እንግሊ
እንግሊዝኛን ጥርት አድርገው አይናገሩም፣
ፈጣን የእንግሊዝኛ ተናጋሪዎችን ንግግር ሰምተው መረዳት አይችሉም። (ቢችሉም እንኳን ብዙ አመት ይፈጅብዎታል።)
እንግሊዝኛ ፅሁፍ አንብበው አይረዱም።
እንግሊዝኛን በጣም ከባድ ቋንቋ አድርገው ያስባሉ።
እራስዎንም እንግሊዝኛ ላይ ጎበዝ እንዳልሆኑ ይቆጥራሉ። እነዚህ አሉታዊ ነገሮች የባህላዊ ትምህርት ቤት ውጤት ናቸው።
በዚች መጽሐፍ ውስጥ የቀረቡትን ዘዴዎች ተግባራዊ ሲያደርጉ፦
የእንግሊዝኛ አነጋገርዎ ይስተካከላል።
እንግሊዝኛ ሲናገሩ አይኮላተፉም።
እንግሊዝኛ አዳምጦ የመረዳት ችሎታዎ ይሻሻላል።
በርካታ ቃላትን ከነአገባባቸው ጭምር ያውቃሉ።
እንግሊዝኛን ያለመንተባተብ በፍጥነት የመናገር ልምድን ያዳብራሉ።
ፈጣን የእንግሊዝኛ ተናጋሪዎችን አድምጠው መረዳት ይችላሉ።
እንግሊዝኛ የመናገር ፍርሀትዎን ያስወግዳሉ!
የተስተካከለ እንግሊዝኛ ይለምዳሉ። ይሄን ሁሉ መሻሻል ግን በቀላሉ አያገኙም! መፅሐፏ ላይ የተጠቀሰውን መማሪያ ዘዴ ሳይታክቱ ተግባራዊ ማድረግ አለብዎት።
ጥሩ የእንግሊዝኛ ተናጋሪ ለመሆን ቃላትን ከመሸምደድ ባሻገር ቀጥለው የቀረቡትን ልምምዶች ማድረግ ያስፈልግዎታል:-
የእንግሊዝኛ ሀረጎችን፣ ሙሉ አረፍተ ነገሮችን፣ ትክክለኛ አነጋገራቸውን እና አገባባቸውን ማጥናት (ምክንያቱም አንድ የእንግሊዝኛ ቃል የተለያዩ አገባቦች አሉት። አገባቡን ወንም ምድቡን በቀየረ ቁጥር ትርጉሙም አብሮ ይለወጣል።)
የእንግሊዝኛ ቀበልኛ እና ፈሊጣዊ አነጋገሮችን ማወቅ
የእንግሊዝኛ ንግግር አድምጦ የመረዳት ልምምድ ማድረግ፣
እንግሊዝኛን ፈረንጆቹ በሚናገሩበት አክሰንት ለመናገር መለማመድ እና
ሀሳብን በፅሁፍ የመግለፅ ልምምድ ማድረግ አስፈላጊ ናቸው።
እነዚህን ክህሎቶች በቀላሉ ማዳበር የሚችሉት፦
እንግሊዝኛን ከራሳቸው ከፈረንጆቹ አንደበት ሲሰሙና አገልግሎት ላይ እየዋለ ያለውን እንግሊዝኛ ሲማሩ ነው። ይህን ደግሞ በቀላሉ በፊልም አማካኝነት መተግበር ይችላሉ።
መጽሐፏ ፊልሞችንና ዘፈኖችን በመጠቀም እንዴት እንግሊዝኛን ባጭር ጊዜ መማር እንደሚችሉ በግልፅ ታስረዳዎታለች።
የእንግሊዝኛ ፊልምና ሙዚቃን በመጠቀም ከዚህ በላይ የተዘረዘሩን ነገሮች በቀላሉ ያዳብራሉ።
መፅሐፏን ሲገዙ እንግሊዝኛዎን ማሻሻል እንደሚችሉ ለራድዎ ዋስትና እየሰጡ ነው።
ይህችን መፅሐፍ ለራስዎ፣ ለልጅዎ ወይም እንግሊዝኛ መማር ለሚፈልግ ወዳጅዎ ይግዙለት። ለሰው ልጅ ትልቁ ስጦታ መጽሐፍ ነው!
በመፅሀፉ ውስጥ
እንግሊዝኛን ለመማር ተፈትነው ውጤታማ የሆኑ ዘዴዎችን ያገኛሉ፤

 • እስከዛሬ እርስዎን ጠፍንገው የያዙ አሉታዊ እምነቶችን በጣጥሰው የሚጥሉ አመለካከቶችን ያዳብራሉ፤
 • የተኛው የመማር ፍላጎትዎ እንደገና ይቀጣጠላል።
 • በዚህ መፅሀፍ ውስጥ ፍርሀትዎን የሚያስወግዱበትን አመለካከት ይይዛሉ።
 • እንግሊዝኛ ሲናገሩ ትክክለኛ የፈረንጆችን አክሰንትና ፕሮነንሲየሽን አስመስለው ይናገራሉ።
 • እንግሊዝኛ አድምጠው የመረዳት ችሎታዎን ያዳብራሉ።
 • ስንፍናዎን ያስወግዳሉ።
 • በትምህርት ቤቶች የሚያወጡትን ከፍተኛ ገንዘብና ጊዜ ቆጥበው እንግሊዝኛን በቀላሉ ይማራሉ!
 • በሚያመጡት ለውጥም ይደመማሉ!
  ዋጋ 20 ብር ብቻ
  መፅሐፉን በስልክዎ ዳንሎድ አድርገው ለማንበብ ቀጣዩን ወየብሳይት ይጎብኙ!
  አንባቢ ትውልድ ራሱን መቀየር ይችላል።
አዲስና ቀላል የእንግሊዝኛ መማሪያ መጽሐፍ
Member Since 24. Cam '21
Verified via:
Email Facebook Mobile Number
Teessoo waamama
Contact via Phone
Contact via Chat
Beeksiisa shakkisiisaa ta'e gabaasa
Cancel
Omishaalee fi tajaajilawwan hedduu Itoophiyaa keessatti argaman bitaa, gurguraa. Huccuulee ykn bu'aalee tekinolojii bifaan adda ta'an, yeroon kan hin daangeessine asitti ni argattu.

Nu bira oomishaalee fi tajaajiloota filatamoo akkasumas hir'ifama gatii filatamaa fi ol'aanaa ta'an kan torban torbanii isiniif ni ergina.