Business ID 3505379

ፍሊንትስቶን ሆምስ

Bole Addis Ababa
About Us

ቢሮዓችን የሚመጡ ብዙ ደንበኞች የሚጠይቁንን ጥያቄዎች እርሶም ቤትዎ ሆነው ሊጠይቁን ይችላሉ
ፍሊንትስቶን በቦሌ፤ በአደይ በሻሌ፤ በዞብል ፤ በካዛንችስ፤ በአዋሬ፤ በኤክስፕረስ ዌይ ፤ በሜክሲኮ ፤ በአርባ ደረጃ፤ ጀሞ፤ ሾላ፤ እንዲሁም በተለያዩ ሳይቶች የመኖሪያ አፓርትመንቶችን ለእርስዎ እንደ አቅሞ እንደ ቤተሰብዎ ለሽያጭ አቅርበናል፡፡

 1. ከዚህም በመነሳት ሳይቶቹ ሲበዙ ለመቆጣጠር አይከብድም ወይ አንዱ ጥያቄ ነው
  ፍሊንትስቶን ኢንጂነሪንግ ባለን የግንባታ ልምድ እነዚህን ሳይቶች ገንብተን ቃል በገባነው መሰረት ቤትዎን ለማድረስ ሌት ተቀን እየሰራን ነው ፡፡ ከዚህም ባለፈ ግን ፍሊንትስን ቤትዎን ሲሸጥልዎ ማህበር በማደራጀት ሲሆን ማህበሩም የሚሰሩትን ቤቶች ሂደት እየተመለከተ ሀሳብ ይሰጣል ፡፡ ሌላው ደግሞ የቤቶቹ የአከፋፈል ሁኔታ የግንባታው ሂደትን የተከተለ በመሆኑ ማህበሩም ሆነ የቤት ባለቤቶች እንደ አማካሪም እንደ ተቆጣጣሪዎቻችንም ናቸው፡፡

 2. ፍሊንትስቶን ይህን ሁሉ መሬት እንዴት ነው የሚያገኘው
  ሀምሳ ሎሚ ለአንድ ሰው ሸክሙ ለሀምሳ ሰው ጌጡ ነው እንደሚባለው
  ብዙ ቤተሰቦች ለአንድ መኖሪያ ከሚያስፈልጋቸው በላይ ባላቸው ሰፋፊ የመሬት ይዞታዎች ላይ በከተሞች አስተዳደር በጸደቀው የማስተር ፕላን ፤ የፕላን ስምምነት አማካኝነት የመልማት ግዴታ ያጣልባቸዋል፡፡ ከዚህም ግዴታዎች ውስጥ አንዱ የከፍታ ግዴታ ነው፡፡ይህም እንደ ማስተር ፕላኑ መሰራት ያለበትን የፎቅ ርዝመት የሚወስን ይሆናል ፡፡ ሌላው ደግሞ የመኖሪያ እና የንግድ ምጣኔ ግዴታ ሲሆን ስልሳ በመቶ ለመኖሪያ ቤት ፤ አርባ በመቶ ለንግድ ሱቆች መሆን አለባቸው የሚል ነው ፡፡ ፍሊንትስቶን እነዚህን ግዴታዎች ከደንበኞች የቤት ፍላጎት ጋር በማጣጣም፤ ተገቢውን ግንባታ በመገንባት ፤ የመሬት ባለመብቱም ተገቢውን ጥቅም አግኝቶ፤ አቅም ላላቸው ደንበኞቻችንም ለሽያጭ በማቅረብ፤ አዳዲስ ነዋሪዎችንም በማካተት ተባባረን ከተሞቻችንን እንደ ማስተር ፕላኑ እንድናስውብ ያግዘናል ፡፡
  ድርጅታዊ መልካም ስነምግባርን በዓርዓያነት እንመራለን !

 3. የተጠናቀቁ አፓርታማዎች አላችሁ
  አዎ አሉን ነገር ግን ከምንሸጣቸው ቁጥር ጋር ሲወዳደር በጣም ጥቂት እና በአንጻሩ ውድ ናቸው፡፡

 4. ግንባታ በጣም ታዘገያላችሁ የሚባለው ለምንድነው
  እንደውም እምንታወቅ የነበረው በፍጥነት በማስረከብ ነበረ ሆኖም ካለፉት አራት አመታት ወዲህ ከገበያው አለመረጋጋት ጋር የመጣ የመጓተት ችግር አለ :: ይህንም ቢሆን ደንበኞችን ባካተተ የተለያዩ የትብብር ዘዴዎች በማስተካከል አሁን አብዛኛው ፕሮጀክቶቻችን መልካም እንቅስቃሴ ላይ ይገኛሉ:: በየፕሮጀክቶቹ እየተደረጉ ያሉትን የትብብር እንቅስቃሴዎች ከስር ከመሰረቱ ለመረዳት የሚከተሉትን ዌብሳይታችንን ይጎብኙ www.flintstonehomes.com

 5. ከባንኮች ጋር ትሰራላችሁ? የባንክ ብድር ታመቻቻላችሁ?
  ድርጅታችን ለረጅም ጊዜ የምንታወቅበት ነገር ከብድር የራቅን መሆናችን ነበር፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን መጠነኛ የስራ ማስኬጃ ብድሮች በመበደር ስራችንን ለማፋጠን ችለናል ፡፡ከዚህም ጋር ተያይዞ ደንበኞች የተራዘመ የክፍያ ስርዓት እንዲጠቀሙ የሚስችል የገንዘብ ፍሰት በድርጅታችን ሊኖር ችሏል ፡፡ በሌሎች ሪልስቴቶች ለደንበኛው የባንክም ሆነ የድርጅት ብድር እንደሚዘጋጅ እንረዳለን በፍሊንትስቶን ግን ያለምንም ወለድ እስከ አምስት አመት በሚቆይ የአከፋፈል ስርዓት የሚስተናገዱ ደንበኞቻችን ቅድሚያ ክፍያ የሚከፍሉት ብር 300 ሺህ ብቻ ነው ፡፡ ቀሪውን በየወሩ በ60 ወራት ያለ ምንም ወለድ ከፍለው ይጨርሳሉ ፡፡ ቤቱ ከዚህ ቀድሞም ካለቀ ተረክበው በመኖርም ሆነ በኪራይ ወርሀዊ ክፍያቸውን ይደጉማሉ ፡፡ በዚህም ምክንያት ደንበኞቻችንን ከባንኮች ጋር ማገናኘት አላስፈለገንም ፡፡

 6. አሁን ለሽያጭ ያሉ ቤቶች ያሉበትን የግንባታ ሂደት የሚያሳዩ ፎቶዎች እንዴት ማግኘት እንችላለን?
  ዌብሳይታችንን ይጎብኙ www.flintstonehomes.com

ፍሊንትስቶን ሆምስ
Member Since 30. Sep '21
Seller Verified by Qefira
Contact Business
Contact via Phone
Contact via Chat
Report This Ad
Cancel
Stay Tuned in with Our Newsletter

We hand-pick our favorites and send you the hottest deals every week!