በኢትዮጵያ አስተማማኝ የመገበያያ ድህረ ገጽ ላይ ይግዙ ፣ ይሽጡ ።
 

ቅድመ ሁኔታ & የግል መብት

የግል ሚስጥርን ስለመጠበቅ
የአገልግሎት ጊዜ

የግል ሚስጥርን ስለመጠበቅ

የግል መረጃዎን ደህንነት መጠበቅ ቅድሚያ የምንሰጠው ነው፡፡ ስለዚህም የምናገኘውን መረጃ በምን መልኩ እንደምንሰበስብ፣ ለምን እንደምንጠቀምበት ለደንበኞቻችን የሚገልጽ ፖሊሲ ነድፈናል፡፡ ፖሊሲውም ከዚህ የሚከተለው ነው፡፡

 • መረጃዎች እንደ አስፈግነታቸው ማጣሪያ ልደረግባቸ ይችላል
 • የምንሰበስበውን መረጃ የምንጠቀመው የዘረዘርናቸውን አላማዎቻችንን ለማሳካት እና ከዚሁ ጋር ተያያዥ ለሆኑ ጉዳዮች ብቻ ይሆናል፡፡ ከዚህ ውጭ ለመጠቀም ግን የተጠቃሚው ፍቃደኝነት አልያም የሕግ አስገዳጅነት ያስፈልጋል፡፡
 • የሰበሰብነውን መረጃ ይዘን የምንቆየው ለፈለግነው አላማ እስክናውለው ድርስ ብቻ ይሆናል
 • የግል መረጃ የምንሰበስበው በሕግ በተፈቀደ፣ በትክክለኛ መንገድ እንዲሁም አስፈላጊ ሲሆንና በግለሰቡ ፍቃድ ብቻ ይሆናል፡፡
 • ከአንድ ግለሰብ የሚሰበሰብ መረጃ ለሚፈለገው ዓላማ ብቻ ጠቃሚ መሆኑ የተረጋገጠ፣ ትክክለኛ፣ የተሟላ እና አዲስ መሆን ይገባዋል፡፡
 • የሰበሰብነው የግለሰብ መረጃ እንዳይሰረቅ፣ እንዳይጠፋ፣ እንዳይለወጥ፣ ኮፒ እንዳይደረግ ወይም ከሚገባው አካል ውጭ ያለ አካል እንዳያገኘው ከፍተኛ ጥንቃቄ ይደረግለታል፡፡
 • የሰበሰብነውን ግለሰባዊ መረጃዎች አያያዝን በተመለከተ ለደንበኞቻችን በዚህ ዙሪያ ያለውን ፖሊሲያችንን በግልጽ እናሳውቃለን፡፡
 • በመሆኑም የንግድ እንቅስቃሴያችንን በእነዚህ መርሆዎች ላይ እንመሰርታለን፡፡ ይህም የሚሰበሰበው የግለሰብ መረጃ ደህንነቱ ከተጋላጭነት የጸዳ እንዲሆን ያደርገዋል፡፡

የአገልግሎት ጊዜ

1. አግባብ

ይህን ዌብ ሳይት ለመጠቀሞ የሚያስችሉ የአጠቃቀም መመሪያዎችና ቅድመ ሁኔታዎችን፣ ተግባራዊ ሊሆኑ የሚችሉ ህጎች እና መመሪያዎችን ለመቀበል ተስማምተዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ በሀገሪቱ ያሉ ተዛማጅ ህጎችን ለማክበርም ሃላፊነት አለብዎ፡፡ ከላይ በተጠቀሱት አግባብ የማይስማሙ ከሆነ ይህን ዌብ ሳይት መጠቀም አይችሉም፡፡ በዚህ ድረ ገጽ ውስጥ የተካተቱት ነገሮች ተፈጻሚነት ባላቸው የቅጂ መብት ህጎች እና በንግድ ምልክት ህግ ጥበቃ የሚደረግላቸው ናቸው፡፡

2. የአገልግሎት ፈቃድ

በዚህ ሳይት ላይ ያሉ መረጃዎችን ለአንድ ጊዜ አገልግሎት በጊዚያዊነት ዳውን ሎድ ወይም ኮፒ ማድረግ ይቻላል፡፡ በቀፊራ' ለግል አገልግለሎት ወይም ንግድ ነክ ላልሆነ ጉዳይ እይታ ብቻ፡፡ይህ ፈቃድ የመስጠት እንጂ የአርእስት ማስተላለፍ አይደለም ፤ በዚህም ፈቃድ ይህን ማድረግ ላይችሉ ይችላሉ

 • በሳይቱ ላይ የሚገኙ መረጃዎችን አስተካክል ወይም ኮፒ አድርግ
 • መረጃዎቹን ለማንኛውም የንግድ አገልግሎት ተጠቀም
 • ማቴሪያሉን ለየትኛውም የንግድም ሆነ ከንግድ ውጭ ያለ አገልግሎት መጠቀም፡፡
 • በቀፊራ ውስጥ ያለ ሶፍትዌርን አሰራር ወደ ኋላ ገልብጦ ለመስራት መሞከር፡፡
 • ከማቴርያሉ ላይ የትኛውንም የኮፒ ራይትና ተዛማጅ መረጃዎችን መሰረዝ
 • ማቴሪያሉን ለሌላ ሶስተኛ ወገን ወይም ሰርቨር ኮምፕዩተር አሳልፎ መስጠት

ከላይ የተዘረዘሩትን ነጥቦች ተላልፈው ከተገኙ ፍቃድዎን ቀፊራ በማንኛውም ጊዜ ሊያቋርጥ ይችላል፡፡ ፍቃድዎ ከተቋረጠ በኋላ የትኛውንም እርስዎ ጋር የሚገኝ የኤሌክትሮኒክስም ሆነ በወረቀት ላይ የሰፈረ መረጃ እንዲያጠፉ እና እንዲሰርዙ እናሳውቃለን፡፡

3. ኃላፊነትን በተመለከተ

በቀፊራ ላይ የሚተዋወቁ እቃዎችን በተመለከተ ቀፊራ በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ መንገድ ምንም አይነት እቃውንና አገልግሎቱን በተመለከተ የብቃት ዋስትና አይሰጥም፣ ኃላፊነትም አይወስድም፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ቀፊራ በድረገጹ ላይ የሚተዋወቁ እቃዎችና አገልግሎቶችን በተመለከተ ለቀረቡ መረጃዎች ትክክለኛነት ማረጋገጫ አይሰጥም፡፡

>

4. ገደብ

ከመረጃ መጥፋት፣ ከኪሳራ እና ከቢዝነሱ መቋረጥ ጋር የሚመጡ ጉዳቶችን በተመለከተ ለሚፈጠሩ ችግሮች ቀፊራና ተባባሪዎቹ ኃላፊነት አይወስዱም፡፡

5. ሊፈጠሩ የሚችሉ ስህተቶችን በተመለከተ

በቀፊራ ላይ የሚወጡ ማስታወቂያዎች የቴክኒክ፣ የአጻጻፍ እንዲሁም የፎቶግራፍ ስህተቶች ሊኖሩባቸው ይችላሉ፡፡ በመሆኑም ቀፊራ በድረገጹ ላይ የሚወጡ ማስታወቂያዎችን ትክክለኛና የተሟሉ ናቸው ብሎ አያምንም፡፡ ቀፊራ በድረገጹ ላይ የሚወጡ መረጃዎችን ያለ ቅድመ ማስጠንቀቂያ የመለወጥ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ቀፊራ በድረገጹ ላይ የወጡ ማስታወቂያዎችን በየጊዜው የማሻሻል ግዴታ የለበትም፡፡

>

6.ተያያዥ ድረ ገጾች

ከቀፊራ ጋር የኢንተርኔት ሊንክ ያላቸውን ድረገጾች ሁሉ ቀፊራ በዝርዝር አልተመለከተም፡፡ በመሆኑም በነዚህ ድረገጾች ላይ ስለሚኖሩ መረጃዎች ይዘት ቀፊራ ኃላፊነት አይወስድም፡፡ አንድ ድረ ገጽ ከቀፊራ ጋር በኢንተርኔት ሊንክ ተያያዘ ማለት ቀፊራ ያንን ድረገጽ ተቀበለ ወይም አንዳች ግንኙነት ፈጠረ ማለት አይደለም፡፡

>

7. የድረገጽ ዝርዘር ፖሊሲውን በተመለከተ

ቀፊራ የድረገጹን ፖሊሲ ሳያሳውቅ መለወጥ ይችላል፡፡ ይህንን ድረገጽ መጠቀም የድረገጹን ፖሊሲ እንደመቀበል ተደርጎ ይቆጠራል፡፡

8. የመንግሥት ህግ

ቀፊራ የሚገዛበት ሕግ
የትኛውም ቀፊራን በተመለከተ የሚቀርብ የሕግ ጉዳይ ከኢትዮጵያ ሕግ አንጻር ይታያል፡፡

አጠቃላይ ዝርዝር ሕጎቹ የድረ ገጹን አጠቃቀም ይወስናሉ፡፡

በራሪ ፅሁፋችንን ይከታተሉ።

በእኛ ዘንድ እጅግ በጣም ተመራጭ የሆኑ ምርቶችና አገልግሎቶችን እንዲሁም የየሳምንቱን ምርጥ ታላላቅ ቅናሾችን እንልክሎታለን።